tg-me.com/elohe19/467
Last Update:
#የህልም_ፍታት_ከአመታት_ወደ_ቀናት
ክተታችን ደርሶ እየመታነው እንገኛለን።
አዲስ ነገርን አስበን ብዙ አስበን ሩቅ አልመን ያዘጋጀነውን አጣፍጠን የሰራነውን ማዕድ ብትቀምሱ ለብርዱም ኩታችሁን ደርባችሁ የኪነ-ጥበብ ማዕድ ላይ ብትቋደሱ እያልን ስንጋብዝ፣
ገጣሚውም ቃሉን ሰድሮ ሙዚቀኛውም ዜማውን ወጥሮ የሰራውን ማዕድ ቅመሱልኝ ብሎ ስለተጣራ ሁላችሁም በጠራነው ክተት ተከታችሁ #ነሐሴ_23_ፒያሳ_በሚገኘው_ከHi5_Coffee_House እንድትገኙ እንላለን።
ያለን ቦተ ውስን በመሆኑ የእሽቅድድም ጉዳይ እና ቀድሞ ቦታ የማስያዙ ጉዳይ ይታሰብበት ልንል እንወዳለን።
ኩታችሁን ደርባችሁ አልያም በሀገር ባህል ልብስ አሸብርቃችሁ ኑልን እኛም ጎንበስ ብለን እንቀበላለን።
ሁላችሁም ግብዣው ይዳረስ ዘንድ #Share እናድርገው
#ከኩታ_የኪነ-ጥበብ_ማዕድ
💚💛❤️
BY መሰልጠን ወይስ መሠይጠን ( ምስል እና ፍልስፍና ቢጤ)
Share with your friend now:
tg-me.com/elohe19/467